And in Jesus Christ, His only Son, our Lord; Who was conceived by the Holy Spirit; Born of the Virgin Mary. We believe in the Holy Spirit; The Holy Apostolic Church, the Communion of Saints; The Forgiveness of sins; The Resurrection of the body; And the life everlasting. Amen.
ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፤ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ፤ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል። ሁሉ በእርሱ ሆነ ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የለም፤በሰማይም ያለ በምድርም ያለ። ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ።